EqubBook · ዕቁብ ደብተር
ግባ

ዕቁብዎን በወረቀት ሳይሆን በስልክ ያስተዳድሩ።

ማን እንደከፈለ፣ ማን እንደቀረ፣ ዕጣ ለማን እንደወጣ — ሁሉም በግልጽ፣ ሁሉም አባላት በስልካቸው ያያሉ። ክርክርና ጥርጣሬ ይቀራል።

ለምን EqubBook?

📒
የጠፋ ደብተር የለምእያንዳንዱ ክፍያ በግብይት ቁጥሩ ይመዘገባል። ሊሰረዝም ሊቀየርም አይችልም።
🎲
ፍትሐዊ ዕጣዕጣው ሁሉም አባላት በሚያዩት መንገድ ይወጣል። አንድ ዙር አንድ ጊዜ ብቻ — ማንም ሊደግመው አይችልም።
📣
ማስታወሻ በአንድ ንክኪላልከፈሉ አባላት በቴሌግራም ወይም በዋትስአፕ ማስታወሻ ይላኩ።
👀
ሁሉም ያያልእያንዳንዱ አባል የዙሩን ሁኔታ፣ የክፍያ ታሪክና አሸናፊዎችን ከስልኩ ያያል።
🔒
ገንዘብ አንይዝምአባላት በቀጥታ ለሰብሳቢው ይከፍላሉ። EqubBook መዝገብ ብቻ ነው።
📱
ምንም አፕ መጫን አያስፈልግምበማንኛውም ስልክ ብራውዘር ይሰራል። በአማርኛና በእንግሊዝኛ።

እንዴት ይሰራል?

ሰብሳቢው ዕቁብ ይፈጥራል — ስም፣ መዋጮ፣ የአባላት ብዛትና ቀን። ባለ 6 ፊደል ኮድ ያገኛል።
አባላት በኮዱ ይቀላቀላሉ — ሊንኩን በቴሌግራም ይልካል፤ ሰብሳቢው ያጸድቃል።
አባላት ይከፍላሉ — በቴሌብር ወይም በባንክ ለሰብሳቢው ከፍለው የግብይት ቁጥሩን ያስገባሉ። ሰብሳቢው ያረጋግጣል።
ዕጣ ይወጣል — ሁሉም ሲከፍሉ ሰብሳቢው ዕጣውን ያወጣል፤ ሁሉም አባላት አሸናፊውን በቀጥታ ያያሉ።

ዋጋ

ለሰብሳቢው
በወር 300 ብር
ለአባላት ነፃ · የመጀመሪያው ወር ነፃ
ነፃ ይጀምሩ
ማሳሰቢያ፦ EqubBook ገንዘብ አይቀበልም፣ አይይዝም፣ አያስተላልፍም። ገንዘቡ ከአባላት በቀጥታ ወደ ሰብሳቢው ይሄዳል። EqubBook የዕቁቡን መዝገብ ብቻ ይይዛል። የዕቁቡ ኃላፊነት የሰብሳቢውና የአባላቱ ነው።